ጉዳዩ እንዲህ ነው: የሰሜኑ ጦርነት ከጀመረ በኋላ በርካታ የፀጥታ አካላት ከሹማምንት ጋር በመሆን የትግራይ ተወላጅ ቤቶችን እየፈተሹ በተለይ ወርቅ እና ብር ይዘርፉ ነበር።

እነዚህ ዜጎች ፍርድ ቤት እንዳይሄዱ እና ለማንም አቤት እንዳይሉ ማስፈራርያ ይነገራቸዋል፣ አለበለዛ በ “ጁንታ” ደጋፊነት አስከፊ ነገር እንደሚጠብቃቸው ስለሚነገራቸው ዝም ብለው ይቀመጣሉ።

ታድያ በዚህ መልኩ ከተዘረፈው ወርቅ ውስጥ እጅግ በርካታ መጠን ያለው ወርቅ የደረሳቸው አንዱ ከፍተኛ ሹም (የፍትህ አካል ከፍተኛ አመራር ነበሩ፣ የህዝብ ተወካይም ናቸው) ቤታቸው በሌባ ይሰበርና ወርቁ በሙሉ ይወሰዳል (በጥቆማ የተደረገ ይመስላል)።

ከዛማ እንዴት አርገው ያስመልሱ ወይም ለፖሊስ እንኳን ያመልክቱ!?

ይህ ሁሉ ወርቅ ከየት መጣ እንዳይባል እና እንዳይጠቆሩ ዝም… ጭጭ… ዋጥ አርገውት እንደቀሩ በቅርብ ጉዳዩን ከሚያውቁ ሁለት ሰዎች ከሰሞኑ ያገኘሁት መረጃ ይጠቁማል።

የሰው ወርቅ አያደምቅ ይልሀል ይሄ ነው።